Tuesday 3 May 2016

ሰሙነ ሕማማትዕለት ዐርብ


የስቅለት ዓርብ ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት ለድኅነተ ዓለም በመስቀሉ ነው፡፡ 
ጊዜንዋም (ዓርብ ምሽት ሦስት ሰዓት) የጌታችን .....መሰጠት (ማቴ.26፥47፣ ዮሐ.18፥3) 
ጊዜ መንፈቀ ሌሊት (ዓርብ ምሽትስድስት ሰዓት) የጌታ መታሰር(ዮሐ.18፥12)
ጊዜ ነግህ (ዓርብ ጠዋት) የጌታ በጲላጦስ ፈት መቆም (ማቴ.22፥1)
ሠለስት (አርብ ቀን ሰዓት)፡- ጌታችን ከጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት (ዮሐ.19፥1፣ ኢሳ.50፥6፣ ሉቃ.23፥13)
ቀትር (ስድስት ሰዓት)፡- ጌታችን እጁና እግሩን ተቸንክረው የተሰቀለበት (መዝ.21፥16፣ መዝ.73፥12፣ ኢሳ.53፥11)
ቅዱስ ማርቆስ በምዕ.15፥25 ላይ ጌታችንን ‹‹በሰቀሉት ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበር፡፡›› ይበል ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ በምዕ.19፥14 ላይ ስድስት ሰዓት መሰቀሉን ገልጦልና፡፡ በዚህ የተለያዩ አይደሉም፡፡ ነገር እንደ ዮሐንስ ነው ቅዱስ ማርቆስ ግን 3 ሰዓት ማለቱ የጌታችን የመስቀሉ ነገር የተበየነው (የተወሰነው) በ3 ሰዓት በመሆኑ ነው የተወሰነበት ሰዓት ይዞ ከተወሰነ መሰቀሉ እንደማይቀር አውቆ 3 ሰዓት አለ፡፡
ተሰዓት (ዘጠኝ ሰዓት) ቅዱስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በገዛ ስልጣኑ የለየበት (ማቴ.27፥50፣ ማር.15፥34፣ ዮሐ.19፥31)
ሠርክ (አስራ አንድ ሰዓት)፡- የጌታችን ቅዱ ሥጋው ከመሰቀል ወደመቃብር የወረደበት (ማቴ.27፥60)
ማስታወሻ፡- ሠርክ በሆነ ጊዜ ምዕመናን ወደቄሱ እየቀረቡ ስግደት እዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡ ቄሱም በወይራ ቅጠል እየጠበጠበ ቀን ሲሰግዱ ከዋሉት ሌላ ተጨማሪ ስግደት ይሰጣቸዋል፡፡ ጥብጣቤው የጌታችን መስቀሉ ነው፡፡ ወይራ መሆኑ ወይራ ጹኑ እንደሆነ የጌታችን መከራ መስቀሉ ከባድ መሆኑ ለማስታወስ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment