Tuesday 26 April 2016

ዕለተረቡዕ/እሮብ/


ሰሙነ ሕማማት ዕለተ ረቡዕ /እሮብ/
ይህ ዕለት ደግሞ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚችሉ ምክር የጀመሩበት ቀን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ዕለቱ" የምክር ቀን" በመባል ይጠራል፡፡" መልካም መዓዛ ያለው" እና "የእንባ"ቀንም ይባላል። ምክንያቱም ማርያም ዕንተ እፍረት ዋጋው ብዙ የሆነ ሽቶ ጌታችንን በመቀባታና ስለ ሀጥያቷ ስቅስቅ ብላ በማልቀሷ ይህንን ስያሜ ተሰጠ። ማቴ 263_13 ማር 14 1_11 ሉቃ 223_6


ሰሙነ ሕማማትና ምስጢሩ ሰኞ

ሰሙነ ሕማማትና ምስጢሩ ሰኞ

  ከትንሣኤ በፊት ያለው ሳምንት ሰሙነ  ሕማማት ይባላል፡፡ ይኸውም በነቢዩ  ኢሳይያስ ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማምነ፣  በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ፤  ሕማማችንም ተሸከመ፤ በእርሱቁስልእኛተፈወስን፡፡/ኢሳ.534-36/  ተብሎ በመንፈስ ቅዱስ ትንቢት የተነገረው ቃል ተፈጸመ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህሳምንት ውስጥ ለድኅነተ ዓለም ሲል በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ የተቀበለውን ጸዋትወ መከራለማስታወስ የወጣ ስያሜ ነው፡፡
ሰኞ፡-
አንጽሖተ ቤተ መቅደስና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ ያድራል፡፡ በማግስቱም ከቢታንያ ሲመጣ ተራበ ወበሳኒታ ወፂኦ እምቢታንያ ርኅበ ወርእየ በለሰ  እምርኁቅ ወባቲ ቈጽለ ወሖረ ይርአይ እመቦ ዘይረክብ ፍሬ በውስቴታ ወበጺሖ
ኀቤሃ አልቦ ዘረከበ ዘእንበለ ቈጽል ባሕቲቱ እስመ ኢኮነ ጊዜሁ ለበለስ፣ ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ ዓይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳችም ፍሬ አላገኘባትም፤ ወአውሥአ ወይቤላ ለዓለም አልቦ ዘይበልዕ ፍሬ እምኔኪ እንከ፣ ከአሁን
ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት፡፡ /ማር. 1111-12/ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፡፡ ፍሬ የተባለች ሃይማት ምግባር ናት፡፡  ከእስራኤል ፍቅርን ሃይማኖትን ምግባርን ፈለገ አላገኘም፡፡ እስራኤል  ሕዝበ እስራኤል መባል እንጂ ደግ ሰውአይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገም ምክንያት እርሱ ከላያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡
አንድም በለስ ኦሪት ናት፡፡ በዚህ ዓለምሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት
ፈጸማት፡፡ እጸ በለስን ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፡፡አንድም በለስ ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሠፊ እንደሆነች ኃጢአትም
በዚህ ዓለም ሥፍራ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፡፡ ኃጢአትም ሲሠሩት ደስ
ያሰኛል፡፡ ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ ወደ እርሷ ሄደ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፣ ኃጥእ ከመባል በቀር በመዋዕሉ ኃጢአት
አለመሥራቱን ለመመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚውሉም በኃጢአት በፍዳ ተይዞየሚቀር አይኑር ለማለት ነው፡፡
ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም በደል ያገኛትን እዳ በደል በእርሱ እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
በመቀጠልም ወደ ቤተ መቅደሰ ሄደ፡፡ ቤተ መቅደስ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተምስያጥ /የንግድ ቤትሁኖ ቢያገኘው
ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ትሰመይ፣ ቤቴየጸሎት ቤት ትባላለች፡፡ እናንተ ግንየወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፡፡ /ማር. 1117-19/ ይህም የሚያሳየው ማደሪያ ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች  ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘንኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልንየሚገልጽ ነው፡፡
በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፣ በሠለስት፣ በስድስት ሰዓትና በተሰዓቱ  ሰዓት መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፡፡ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ ምክንያቱም የደረሰበትን መከራ ኀዘኑንና 5500 ዘመን የሰው  ልጅ በጨለማ ሕይወት ይኖርእንደነበር ለማዘከር ነው፡፡
"ኪርያላይሶን አቤቱ ይቅር በለን "

ማቴ 21: 1

ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ፡-

ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ፡-

የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም ሹመትን ወይምሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፡፡
ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ሥልጣን ታደርጋለህየሚል ነበር ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረችከሰማይ ወይስ ከሰውአላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትምይለናል፡፡ ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው፡፡ ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፡፡ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ፡፡ ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው፡፡በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ\ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምርነው፡፡


"ኪርያላይሶን"